ካሊ የክሪስማሱ አባጨጓሬ
በአንድ ወቅት ቤተልሔም በሚባል ቦታ ካሊ ተብሎ የሚጠራ አባጨጓሬ ይኖር ነበር፡፡ እርሱ ከችግር ለመውጣት የራሱን ጥረት የሚያደርግ ጥሩ አባጨጓሬ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ምርጫዎችን ስለሚያከናውን ይህ ለእርሱ ከባድ ነበር፡፡
አንድ ቀን ጥቂት የሚበላ ምግብ ለመፈለግ ወጣቱ አባጨጓሬ ከተራራ ጫፍ ላይ ለመውጣት ይወስናል፡፡ ተራራው ጫፍ ላይ ሲደርስ በብዙ ዓለቶች የተከበበ ትልቅ ዋሻ መኖሩን ይረዳል፡፡ ካሊ በግኝቱ ይደሰታል፡፡ ወደ ጥቁር ዋሻ መውጣቱ ጥሩ ሀሳብ መሆኑን እርግጠኛ ባይሆንም ወደ ውስጥ ለመግባት ይወስናል፡፡
ካሊ በዋሻ ውስጥ በጣም ቅዝቃዜ እና ብቸኝነት ይሰማው ጀምሯል፡፡ እርሱ ከአሁን በፊት ጭለማ በሆነ ቦታ ውስጥ እና ብቸኛ ሆኖ የማያውቅ በመሆኑ ምክንያት በጣም ተናዷል፡፡ በፍጥነትም ወደኋላ ለመመለስና ለመውጣት ይወስናል፡፡እንዳለመታደል ሆኖ ትንሹ አባጨጓሬ በየት በኩል እንደወጣ በማያስታውስበት ሁኔታ በሆኑ ዓለቶች ላይ ይወድቃል፡፡ ወደግራ ወይ ወደቀኝ ይመለስ? ካሊ የሚያውቀው ነገር የለም!
በጣም ረጅም ለሆነ ጊዜ በሚመስል መልኩ በዋሻ ውስጥ ከጠፋ በኋላ ካሊ በፍፁም መውጣት እንደማይችል አሰበ፡፡ እርሱ ጭለማ ውስጥ ስለጠፋ ለራሱ እንዲህ አለ፤ "እዚህ አስፈሪ ዋሻ ውስጥ በፍፁም ያልገባሁ ቢሆን እመኛለው"፡፡ ካሊ ምን እንደሚሰራ ባለማወቁ ምክንያት ፍርሀት ተሰምቶታል፡፡
ካሊ ማንም ሊያገኘው እንደማይችል ሲያስብ ተስፋ ወደመቁረጡ ደርሷል፡፡ በዛች ቅፅበት የአህዮችን፣ የላሞችንና የበጎችን ድምፆች ይሰማል፡፡ከዚህ በኋላ ብቸኝነት ስለማይሰማው እነዚህ ድምፆች ደስተኛ አድርገውታል፡፡
በቤተልሔም ውስጥ ቀዝቃዛ እና ነፋሻማ የክረምት ሌሊት ስለነበር እረኞች እንስሳቱን ዋሻው ውስጥ እንዲተኙ ለማምጣት ወስነዋል፡፡ ልክ ሰዎቹ ከነሻማዎቻቸው ሲገቡ፤ ካሊ ዋሻው በጣም ትልቅ እንደነበር ማየት ችሏል፡፡ በትልቁ ክፍል ውስጥ ለእንስሳቶቹ ሞቅ ያሉ መኝታዎች እንዲሆን የገለባ እስሮችን ጎዘጎዙላቸው፡፡ እንደ ሌሎች እንስሳቶች አባጨጓሬውም ከረጅም ቀን በኋላ ተኝቶ ነበር፡፡ ወዲያው እያንዳንዱ በፍጥነት ተኝተው ነበር፡፡
በጠዋት እረኞቹ እንስሳቶቹን በመቀስቀስ በፍጥነት ዋሻውን ለቀቁ፡፡ ካሊ በሚነቃበት ወቅት እነርሱ ሄደው ነበር፡፡ እንስሳቶቹና እረኞቹ በጠዋቷ ፀሀይ ሙቀት ለመደሰት በጠዋት ተነስተዋል፡፡ "አሁን ምን ላድርግ?" አለ ካሊ፡፡ ቀሪው ህይወቱን ማሳለፍ የሚኖርበት በዚህ ቦታ ውስጥ እንደሆነ ተሰማው፡፡
ከዚያም ሰዎቹ ከክረምቱ ሌሊት እንስሳቶቻቸውን ለመጠለል መመለስ ጀምረዋል፡፡ ካሊ ሌሎች ከእርሱ ጋር በዋሻው ውስጥ የነበሩ በመሆናቸው የተሻለ ስሜት ቢሰማውም፤ ይህንን ትልቅ ዋሻ በፍፁም መልቀቅ እንደማይችል ሲያውቀው ያለቅሳል፡፡ ምንም እንኳን እንስሳቶቹ እሰከአሁን እዚህ ቢኖሩም ሰዎቹንና እንስሳቶቹን በመከተል ከዚህ ጨለማ ለመውጣት እግሮቹ አጫጭር ነበሩ፡፡
ልክ ለራሱ የሀዘን ስሜት ሲሰማው የተለየ ነገር ተከሰተ፡፡ ዮሴፍ የተባለ ሰው ወደ ዋሻው ገባ፡፡ እርሱም በገለባው መኝታ ማዘጋጀት ጀመረ ነገር ግን ለእንስሳቶች አልነበረም፡፡ ይህ መኝታ ልጇን ለመታቀፍ ለተቃረበችው እና ማረፍ ለሚያስፈልጋት ለእጮኛው ድንግል ማርያም ነበር፡፡
ማርያም አዲስ የተወለደውንና ስሙን ኢየሱስ ያለችውን ወንድ ልጇን ስትይዝ አባጨጓሬው በስሜት ይመለከት ነበር፡፡ ይህ ልጅ በብርሀንና በፍቅር የተሞላ ነበር፡፡ ካሊ ወደ ኢየሱስ ሲመለከት እርሱ እንደእርሱ ብቸኛ እና ፈሪ አልነበረም፡፡
በዛው ሌሊት ሌሎች እረኞች ወደ ዋሻው በመግባት ለሕፃኑ ኢየሱስ ዝማሬዎችን መዘመር ጀመሩ፡፡ ጨለማ የነበረው ዋሻ አሁን እያንዳንዱን ሰው የሰላምና የደስታ ስሜት እንዲኖረው በሚያደርግ ብርሀን ተሞላ፡፡ ከዚያም የሚያበራ ኮከብን የሚከተሉ ሦስት አዋቂ ሰዎች (ሰብዓ ሰገል) ለሕፃኑ ኢየሱስ የክሪስማስ ስጦታ ለመስጠት መጡ፡፡ ወርቅ፣ እጣን እና ከርቤ ሰጡት፡፡
እርሱን ለመጎብኘት በሚመጡት ሁሉ ብዙ ደስታን በሚያመጣው ሕፃን፤ ካሊ በአድናቆትና በአክብሮታዊ ፍርሀት ተሞላ፡፡ ለሕፃኑ ኢየሱስ የሚሰጠው ስጦታ ስላልነበረው አሁንም አዝኗል፡፡ እንዲህ ሲል አሰበ "እኔ በዚህ ዋሻ ውስጥ የጠፋው ብቸኛው አባጨጓሬ ስሆን ብርሀኑን ለሰጠን ሕፃን ምን አይነት ስጦታ ልስጠው?" አሰበ፣ እናም አሰበ እናም ተጨማሪ አሰበ፡፡
"እኔ አውቃለው!" አለ ካሊ፡፡ ለኢየሱስ በሚሰጠው ስጦታም ተደሰተ፡፡ እንደ ክሪስማስ ስጦታ ራሱን ለመጠቅለል ወሰነ፡፡ በጥንቃቄ የእጭ ሽፋን በመስራት ራሱን በመጠቅለያ ውስጥ ጠቀለለ፡፡ ካሊ ጊዜውን በሙሉ የሚያስበው እንዴት ስጦታውን ለኢየሱስ መስጠት እንደሚፈልግ ብቻ ነበር፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ካሊ ከእጭ ሽፋኑ ወጣ፡፡ በዚያን ጊዜ ነበር እርሱ የክሪስማስን ተዓምር ያገኘው፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ እርሱ በዋሻ ውስጥ ተይዞ የነበረ ብቸኛ አባጨጓሬ አይሆንም፡፡ እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው፤ ቢራቢሮ ከሚያስደንቅ ጥንድ ባለ ልብ ቅርፅ ክንፎች ጋር፡፡
ካሊ ከጭለማው ውስጥ ወደ ብርሀኑ ሲበር ፈገግታ በፊቱ ላይ ነበር፡፡ ትክክለኛውን ምርጫ እንዳከናወነ እና ኢየሱስም በእርሱ ስጦታ እንደተደሰተ አውቋል፡፡ በአየር ላይ ቢራቢሮ እየበረረ ሲታይ ልባችን ለኢየሱስ እንድንሰጥ ያስታውሰናል፡፡
ተፈፀመ